የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድ ቁጥጥር ባለሥልጣን

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ ስር ከ2008 ዓ/ም ጀምሮ ከተቋቋሙት ተቋማት መካከል አንዱ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሰልጣን ነው:: በከተማው ውስጥ በከፈታቸው 11 ቅ/ጽ/ቤቶች ዛሬውኑ ጉዳዮን ይጨርሱ፡፡

የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን

የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣንየአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን

ራዕይ(Vision)

የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ብቃትን በማረጋገጥ በ2022 ዓ/ም ህብረተሰቡ በአሽከርካሪና ተሸከርካሪ እየደረሰ ካለው አደጋ ተጠብቆ ማየት፡፡

ተልዕኮ (Mission)

የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ተቋማትን በማደራጀት፣ የክትትልና ቁጥጥር አግባብን በማጠናከር፣ አፈፃፀማቸውን በማሳደግ፣የአገልግሎት አሰጣጡንና የመረጃ አያያዝ ስርዓትን በማዘመን፣ጥናትና ምርምር በማካሄድ ውጤታማ የአሽከርካሪ ተሽከርከሪ ፈቃድና ብቃት ማረጋገጥ፡፡

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

⦁ ተላላፊ መመለሱን ማረጋገጥ፡፡ ⦁ ተላላፊ ለመዉሰድ የቀረቡ መሰረታዊ ሰነዶች መሟላታቸዉን ማረጋገጥ ⦁ ለመጀመሪያ ምዝገባ የሚመጣ ተሽከርካሪ ለጭነት አወሳሰን የነጠላ ክብደት መመዘን የሚገባው ከሆነ የተመዘነበት ማረጋገጫ ሰነድ /የሚዛን ወረቀት/፡፡ ⦁ ተሸከርካሪው ዋጋ ካሽ ሪጅስተር ደረሰኝ/Invoice/ ከዲክላራሲዮን ዋጋ በማነፃፀር ከፍተኛ በሆነዉ የቴምብር ቀረጡን 2% ማስከፈል፡፡ ⦁ የ3ተኛ ወገን የጸና የመድን ዋስትና ⦁ ከ6 ወር ወዲህ የተነሱት 2 ጉርድ ፎቶ፤ ቴምብር ⦁ ተወካይ ከሆነ ሊብሬዉ በቴምብር ይሰራል፡፡ ⦁ የአገልግሎት ክፍያ በማስከፈል ሰሌዳ፣ ሊብሬ፣ ቦሎ መስጠት፡፡
⦁ ባለንብረት ወይም ተወካይ ከውክልና ሠነድና የታደሰ መታወቂያ/መንጃ ፍቃድ ⦁ የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር /ሊብሬ/ ⦁ የምርመራ ሰርተፊኬት የቆይታ ጊዜ ተሸከርካሪው ከተመረመረበት ቀን ጀምሮ ቦሎ ለመውሰድ ለኢ.ት ሰሌዳ 30 ቀን ለአ.አ 20 ቀን ያላለፈዉ ⦁ ዓመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ በሚካሄድበት ወቅት የምርመራ ተቋሙ ሁለት ቴክኒሽያኖችን እና የተቋም ኃላፊ መፈረማቸው ⦁ ተሽከርካሪው ወደ ምርመራ ቦታ መጥቶ የተመረመረ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ የተሸከርካሪዉን ሰሌዳ በግልጽ የሚያሳይ ምስል ፕሪንት አውት ላይ ፎቶግራፍ ከሚነበብ ሰሌዳ ጋር መኖሩ ⦁ ለግል ንግድ በንግድ ፈቃዱ ስም፤ ለንግድ በተሽከርካሪው ሰሌዳ፣ የሻንሲና የሞተር ቁጥር የተገለጸ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ወይም የግብር ክሊራንስ መኖር ⦁ የ3ኛ ወገን ኢንሹራንስ የገባበት ዉል መኖሩን ⦁ የመንገድ ፈንድ ክፍያ ሠርቲፊኬት መኖሩን እና ⦁ ቀረጥ ነጻ የገባ የአካል ጉዳተኛ ተሽከርካሪ ከሆነ ከማህበራዊ ዋስትና መ/ቤት ደብዳቤ ⦁ የቴክኒክ ምርመራ ባለፈው ዓመት ምርመራ ካላደረገ የቅጣት ጨምሮ የዘመኑ ቦሎ ክፍያ ሌሎች የአገልግሎት ክፍያዎችን መክፈሉ ተረጋግጦ ቦሎ ይሰጣል፡፡ ቅጣት በየ15 ቀኑ ብር 100 ነው፡፡
1. ኮድ 01፡- ለታክሲ አገልግሎት</br> 2. ኮድ 02፡- ለቤት አገልግሎት 3. ኮድ 03፡- ለንግድና ለግል ንግድ አገልግሎት (ንግድ ፍቃድ ላለቸው ለመንግስት ልማት ድርጅቶችና ፕሮጀክቶች) 4. ኮድ 04፡- ለመንግስታዊ ተቋማት 5. ኮድ 05፡- ለሃይማኖት ተቋማት፣ ለሀገር በቀል ልዩ ልዩ ድርጅቶችና ማህበራት 6. ጊዜያዊ ሠሌዳ/ ተላላፊ ...

እባክዎን አስተያየትዎን ይስጡን

በተቋሙ ያገኙት አገልግሎት ምን ይመስል ነበር?

የአስተያየት ቅጽ









የእርሶ አስተያየት እራሳችንን እንድንፈትሽ ይረዳናል፡፡

ምንአዲስ ነገር አለ?

አዳዲስ ዜናዎች

የቅሬታ ቅጽ