9ኛው ጉብኝታዊ ግምገማ በአራዳ ቅርንጫፍ ተደርጓል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን 9ኛውን የቅርንጫፍ ጉብኝታዊ ግምገማ በአራዳ ቅርንጫፍ አድርጓል ።
የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ደረጀ መንገሻ ፦ የአግልግሎት ቅድመ ሁኔታወች ግልፅ እና ተደራሽ በሆነ መልኩ በቴክኖሎጂ የተደገፈ መሆኑን ፣ የወረፉ ማስጠበቂያ ማሽን መኖሩ እና ተገልጋይ በተመቸው ቦታ ሆኖ ወረፉውን የሚያውቅበት ሲስተም መዘርጋቱን ፣ አገልግሎቱ የት ተጀምሮ የት እንደሚያልቅ የሚያመላክት ሲስተም ፈጥረው ተግባራዊ ማድረጋቸውን አስጎብኝተዋል ።
ስራ አሥኪያጁም አያይዘው የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራቸው ፦ ተገልጋዩን ለከፍተኛ መጉላላት ሲዳርግ የነበረው የመረጃ ማፈላለጊያ ፣ የተገልጋይ እርካታ መለኪያ እና አገልግሎት የሰጠውንም ባለሙያ የማገልገል አቅምና ስነምግባር በደረጃ የሚለካ ፣ የስራ ክፍሎች የስራ ቅብብሎሽ የተገልጋይ ምልልስን ያስቀረ እና ተጠያቂነትን ያሰፈነ እና የመዝገብ ቤት እና የፍይል አደረጃጀት ማዘመን ላይ ችግር ፈች መሆኑን ገልፀዋል።
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ስራ አሥኪያጅ ደሳለኝ ተረፈ (ኢንጂነር) የሪፎርሙ ውጤታማነት የሚለካባቸ አመላካቾችን በቅርንጫፉ መተግበራቸው እንዳስደሰታቸው ገልፀው ፦ ለውጥን በማመን እና የለውጥ ምክንያት በመሆን ውጤታማ ስራ የሰሩትን የቅርንጫፉ ሰራተኞች እና አመራሮች አመስግነዋል።
በጉብኝታዊ ግምገማው ፦ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አሥኪያጅን ጨምሮ 3ቱ የዘርፍ ም/ዋና ስራ አሥኪያጆች ፣ የዋና ስራ አሥኪያጁ አማካሪ፣ የ12ቱም ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ተገኝተዋል።