#የሰው_ተኮር_ስራዎቻችን_የለውጡ_ውጤታማነት_ማሳያዎች_ናቸው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን 15 የአቅመ ደካማ ቤቶች ዕድሳትን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አስጀምሯል።

''ለውጥ ከቅርቡ የስራ እና መኖሪያ አካባቢ ይጀምራል'' በማለት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጭነት ተጀምሮ  ፕሮግራሙ በሀገር ደረጃ የሰው ህይወት እና አካባቢን በመቀየር በርካታ ውጤት አስገኝቷል።
 
ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ለአቅመ ደካሞች እና አረጋዊያን እንዲደርስ የተቀረፀው ፕሮግራም የብዙዎችን ህይወት በዘላቂነት ማሻሻሉን፣ ዘመናዊ ከተማ በመገንባት የአካባቢዎችን ገፅታ መቀየሩን አንስተው፦ የዚህ አካል የሆኑት እነዚህ ቤቶች በጥራት እና በፍጥነት እንዲታደሱ የትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊዎች አቶ ያብባል አዲስ በፕሮግራሙ ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ደሳለኝ ተረፈ (ኢ/ር) በበኩላቸው፦ ያለንን ማካፈል፣ ከራስ አልፎ ለሰው ማሰብ፣ ለሰው የመኖር ልምምዳችን እያደገ መጥቷል። በመሆኑም ዛሬ የምናድሳቸው ቤቶች፦ የዜጎችን ህይወት ወደ ኋላ የሚመልሱ እና የተፋፈጉ ቤቶችን መልሶ በማልማት ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት ከተማ የመገንባቱ ሂደት አካል መሆኑን ተረድተን፦ በቅርቡ ጥራት ያለው ቤት ሰርተን እናስረክባለን ብለዋል።

እንደ ዋና ሥራ አስኪያጁ ገለፃ 15ቱን ቤቶች ለማደስ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው በገንዘብ ላገዙና ላስተባበሩ ምስጋና አቅርበዋል ።

በፕሮግራሙ ላይ፦ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ያብባል አዲስን ጨምሮ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የማእከል እና የቅርንጫፍ አመራሮች፤ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና፣ የክፍለ ከተማው እና የወረዳ አመራሮች፣ በጎፈቃደኞች፣ የቤት ዕድሳት ተጠቃሚዎች ተገኝተዋል።