ለተሽከርካሪ አገልግሎቶች ቅድመ ሁኔታዎች
አመታዊ የተሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ /ቦሎ/
ቦሎ የማስደረግ ሂደት
1.የተሸከርካሪ የቴክኒክ ምርመራ ማስደረግ፤
2.የመንገድ ፈንድ ክፍያ መፈፀም፤
3.አሸከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ቅ/ጽ ቤት ያለውን ሂደት በመፈፀም ቦሎ መውሰድ።
ከባለጉዳይ የሚጠበቁ ሰነዶች
-የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር /ሊብሬ/፤
-ዓመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ ከፈፀሙበት ተቋም የሚሰጥ የምርመራ ሰነድ፤
-የ3ኛ ወገን ኢንሹራንስ የተገባበት ሰነድ፤
-የመንገድ ፈንድ የተከፈለበት ሰነድ፤
ተጨማሪ
ለግል ንግድ ተሽከርካሪ ከሆነ በንግድ ፈቃዱ ስም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ወይም የግብር ክሊራንስ፤
ለንግድ ተሽከርካሪ ከሆነ በተሽከርካሪው ሰሌዳ፣ የሻንሲ እና የሞተር ቁጥር የታደሰ ንግድ ፈቃድ ወይም የግብር ክሊራንስ።
ማስታወሻ
-ሊብሬው በዕዳ የታየዘ ከሆነ ከአጋጁ የተፃፈ የስምምነት ደብዳቤ መቅረብ አለበት፤
-የተሽከርካሪ ምርመራ ሲያስደርጉ፣ የምርመራ ሰነዱ በተቋሙ ሁለት ቴክኒሺያኖች እና በተቋሙ ሃላፊ መፈረም አለበት፤
-በተሽከርካሪ ምርመራ ወቅት ተሽከርካሪው ወደ ምርመራ ተቋሙ መምጣቱን የሚያረጋገጥ የተሸከርካሪውን ሰሌዳ በግልፅ የሚያሳይ ፎቶ በምርመራ ሰነዱ ላይ መያያዝ አለበት፤
-ለአዲሰ አበባ ሰሌዳ፣ ምርመራ ከተደረገ 20 ቀን ማለፍ የለበትም፤
-ለኢቲ ሰሌዳ ምርመራ ከተደረገ 30 ቀን ማለፍ የለበትም፤
-ተሽከርካሪው ያለፈውን ዓመት የቴክኒክ ምርመራ ያላደረገ ከሆነ ቅጣትን ጨምሮ የዘመኑን የቦሎ ምርመራ ክፍያ ይፈፅማሉ፤
-ቦሎ ማድረግ ባለቦት ቀን ሳያደርጉ ከቀሩ ለዘገዩበት እያንዳንዱ 15 ቀን የአንድ መቶ ብር ቅጣት ይከፍላሉ፤
-ተሽከርካሪው ከቀረጥ ነፃ የኮድ ሁለት የአካል ጉዳተኞች ከሆነ ከሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የድጋፍ ደብዳቤ እንዲያቀርቡ ይጠበቃል
አዲስ ተሽከርካሪ ምዝገባ
መታወቂያ (መ/ፈቃድ ወይም ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ከፖስፖርት ጋር
ውክልና ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ መ/ፈቃድ ፓስፖርት
ከመ/ቤት ወይም ከድርጅት የተወከለ ከሆነ የድርጅቱ የውክልና ደብዳቤና የድርጅቱ መታወቂየ
ኦርጅናል የጉምሩክ ዲክላራሲዬን
ሁለት ጉርድ ፎቶ ቴምብር ( በውክልና ከሆነ ፎቶ አያስፈልግም)
የታደሰ የተሸከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ እና የአስመጪነት ፈቃድ, የማስገቢያ ፈቃድ
የተሽከርካሪ መመርመሪያ ቅፅ /ሮዝ ወረቀት/
ደረሰኝ /invoice/ ከባለንብረት ስም ከአታችመንት ጋር የእጅ በእጅ ሽያጭ ከሆነ የደረሰኝ ህትመትና የማስታሚያ ፈቃድ ከጉምሩክ በደረሰኝ መነሻ ቁጥር የተፈቀደበት ደብዳቤ
ሶስተኛ ወገን የፀና የመንገድ ፈንድ
የአገልግሎት ለውጥ /የሰሌዳ ኮድ ለውጥ/
ተሽከርካሪው በአካል ቀርቦ ምርመራ ማድረግ
የንግድ ከሆነ ኮድ 03 ኮድ 01 ከሆነ ከገቢዎች ክሊራንስ
ሙሉ የመድህን ሽፋን
ግምት
ሻጭ እና ገዥ በአካል መቅረብ /መታወቂያ/ ኮፒ
የውል ስምምነት የተፈራረመበት
ሊብሬ /የባለቤትነት ማረጋገጫ
የዋጋ ግምት የሚያገለግለዉ ለ6ወር ብቻ ነዉ
ተሽከርካሪው በአካል መቅረብ አለበት
ስም ዝውውር
ከሰነዶች ማረጋገጫ የፀደቀ 2% የተከፈለበት ደረሰኝ የስም ዝውውር ሰነድ
ለኮድ 03 ለኮድ 01 ከገቢዎች ክሊራንስ
ሁለት ጉርድ ፎቶ /የገዥው በውክልና ከሆነ ቴምብር
የዘመኑን ቦሎ ያደረገ
ሶስተኛ ወገን
በጨረታ የሚሸጡ ተሽከርካሪዎች በተመለከተ
ተሽከርካሪው ቀረጥ ያለበተና ዲክላራሲዬን የሌለው ከሆነ አዲስ በገዥው የተሰራ ዲክላራሲዩን ከገቢዎች ና ጉሙሩክ
የጨረታ አዋርድ ደብዳቤ
ጨረታ የወጣበት ቀን፣ ቁጥር ፣የጋዜጣው ስም የአሸናፊው ስም፣ የተሽከርካሪው ሻንሲ እና ሞተር ቁጥር ጨረታውን ያሸነፈበት ዋጋ፣የክፍያ ደረሰኝ
ድርጅት ከሆነ ከመንግስት መ/ቤት ውጭ ከሆነ ሻጭ ድርጅት ሰው ይወክላል
ከአገልግሎት ውጪ ከሆነ/ኢንሹራንስ /ባለንብረቱን ይወክላል
እገዳ ማንሳት
ከህጋዊ ድርጅቶች ማንሻ ደብዳቤ የታገደበት ምክንያት የዕዳው መጠን የሚገልጽ
የተሽከርካሪውን ሰሌዳ በትክክል መግለፅ ኮድ፣ የሰሌዳ ቁጥሩን አ.አ ወይም ኢ.ት መሆኑን
የባለጉዳዩን ማንነት የሚያረጋግጥ መታወቂያ
እግድ ማገድ
ከአገደዉ አካል ህጋዊ ደብዳቤማምጣት
የዕዳው መጠን/ ምክንያት
የተሽከርካሪው ሰሌዳ ቁጥር ኮድ ፣ አ.አ፣ ኢ.ት፣ መሆኑን መግለፅ
ማንነትን የሚገልጽ መታወቂያ
የተሽከርካሪ ፋይል በዝውውር /ከአ/አበባ ወደ ክልሎች /
ኮድ 03/01- ከሆነ ከገቢዎች ክሊራንስ
ሊብሬ የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር
የዘመኑን ቦሎ ማድረግ
ቀረጥ ነፃ ማንሳት
(ሊብሬ)
በውክልና ከሆነ ውክልና እና መታወቂያ
በባለንብረቱ ስም የተዘጋጀ ዜሮ ዲክላሬሽን ከ ጉምሩክና ገቢዎች
ሁለት ጉርድ ፎቶ
ውል ማፍረስ
ገዥ እና ሻጭ የተፈራረሙበት ውል ማፍረሻ
ከዚህ ቀደም የተወሰደውን የግምት ወረቀት
የተሽከርካሪ መረጃ ማስተካከያ አገልግሎት
በውክልና ከሆነ ውክልና እና የታደሰ መታወቂያ / የባለንብረቱ የመኖሩያ አድራሻ የሚገልፅ መንጃ ፈቃድ ፣ፓስፖርት ወይም መታወቂያ
ተሽከርካሪ በአካል ማቅረብ
ከክልል ወደ አዲስ አበባ ፋይል ዝውውር
በፖስታ ቤት የመጣ የዝውውር ፋይል 6 ወር ባልበለጠ ጊዜ ዉስጥ
በውክልና ከሆነ ውክልና እና የታደሰ መታወቂያ አድራሻ የሚገልፅ
ለንግድ ተሽከርካሪዎች የአድራሻ ለውጥ ክሊራንስ (ከገቢዎች)
የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር (ሊብሬ) እና ሰሉዳ (ታርጋ)
ሁለት ጎርድ ፎቶ ግራፍ
ተሸክርካሪዉ በአካል መቅረብ አለበት
ስርዝ ድልዝ የሌለዉ የማዘዋወሪያ ቅፅ
የአካል ለውጥ አገልግሎት
ተሽከርካሪ በአካል ማቅረብ
ሁለት ጉርድ ፎቶ
የአካል ለውጥ የሚያደርገው ድርጅት ወይም ጋራዥ
የታደሰ ንግድ ፍቃድ በርጥብ መሀተብ የተረጋገጠ
የብቃት ማረጋገጫ
የተከፈለበት ደረሰኝ
የሞተር ለውጥ ከሆነ ዲክላራሲዮን እና ኢንቮይስ (ደረሰኝ)
ለጠፋ ሊብሬ
ከባለጉዳይ የሚጠበቅ
መኪና በአካል መቅርብ
አገልግሎት ጠያቂው የግለሰብ ተወካይ ከሆነ የታደሰ መታወቂያ እና በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ፤
አገልግሎት ጠያቂው የድርጅት ተወካይ ከሆነ ድርጅቱ ለአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን የተፃፈ ድብዳቤ እና የተወካዩ የስራ መታወቂያ፤
ሊብሬው ስለመጥፋቱ የፖሊስ ማስረጃ፤
ተገቢውን ክፍያ እና ሂደት በመፈፀም ሊብሬው ስለመጥፋቱ በጋዜጣ ላይ ማስታወቂያ ማስወጣት፤
ማስታወቂያው አየር ላይ ለ15 ቀን ከቆየ በኋላ ጋዜጣውን ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ማቅረብ፤
የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም።
ለጠፋ ቦሎ
ከባለጉዳይ የሚጠበቅ
1. አገልግሎት ጠያቂው የግለሰብ ተወካይ ከሆነ የታደሰ መታወቂያ እና በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ የውክልና ሰነድ፤
2.አገልግሎት ጠያቂው የድርጅት ተወካይ ከሆነ ድርጅቱ ለአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን የተፃፈ ድብዳቤ እና የተወካዩ የስራ መታወቂያ፤
3.የተሽከርካሪው ሊብሬ፤
4.ለጠፋ ቦሎ ከሆነ ቦሎው ስለመጥፋቱ የፖሊስ ማስረጃ፤
5.ለተበላሸ ቦሎ ከሆነ የተበላሸውን ቦሎ፤
6.የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም።
ለተበላሸ ሊብሬ
የተበላሸውን ሊብሬ
ጉርድ ፎቶ ግራፍ (ሁለት)
ውክልና ከሆነ ውክልናና መታወቂያ ከሆነ ቴምብር
መኪና በአካል መቅረብ
ለተበላሸ ቦሎ
የተበላሸውን ቦሎ
ውክልና ከሆነ ውክልናና መታወቂያ
ሊብሬ( የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር)
የመረጃ/ደብዳቤ አገልግሎት
የተጠየቀበት ደብዳቤ
ውክልና ከሆነ ውክልና መታወቂያ
ለጠፋ ሰሌዳ (ታርጋ)
ውክልና ከሆነ ውክልናና መታወቂያ
የፖሊስ ማስረጃ የጠፋ መሆኑን
የሰሌዳ ስረዛ (ከአገልግሎት ውጭ)/ በአደራ ማስቀመጥ
የሚመልስበት ወይም በአደራ የሚያስቀምጥበትን ምክንያት የሚገልፅ በደብዳቤ
ከአደጋ ነፃ የፖሊስ ማስረጃ
ተሽከርካሪው በቴክኒክ ክፍል ማረጋገጥ
ለንግድ ተሽከርካሪ ክሊራንስ (ከገቢዎች )
ውክልና ከሆነ ውክልናና መታወቂያ
የቦሎ አገልግሎት ክፍያ ካለ እንዲከፍል ማድረግ
ሰሌዳና ሊብሬ መመለስ
በአደራ ለማስቀመጥ ከ 2 አመት በፊትና ከ5 አመት በሓላ የሰሌዳ ይመለስኘ ጥያቄ ማቅረብ አይችልም
ለአሽከርካሪ አገልግሎቶች ቅድመ ሁኔታዎች
የኢንተርናሽናል የአሽከርካሪ የብቃት ማረጋገጫምትክ ለመስጠት
-ፓሰፖርት እና ቪዛ 2ኮፕ
-2 ጉርድፎቶ 3 X 4
-የአሽከርካሪብቃት ማረጋገጥ ፈቃድ(መንጃ ፈቃድ) 2 ኮፕ
የአሽከርካሪዎች የዕድሜ ማስተካከያ
.ህጋዊ የሆነ የልደት ሰርተፍኬት
.የቀድመውን የአሽከርካሪ ብ ቃት ማረጋገጥፈቃድ(መንጃ ፈቃድ)
የአሽከርካሪዎች የስም ለውጥ ለሚፈልጉ
.ከፍርድ ቤት ለስም ለውጥ የተሰጠ ውሳኔ
.የቀድመውን የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጥ ፈቃድ(መንጃ ፈቃድ )
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ፋይል(መንጃ ፈቃድ) ከአዲስ አበባ ወደ ክልል ለመላክ
ወደክፍለሀገርየምዛወርበትንምክንያትየምገልጽ አግባብነት ያለውደብዳቤ
ሳይታደስ ጊዜ ያለፈበት አሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ (መንጃ ፈቃድ)
.ጊዜ ያለፈበትን አሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ (መንጃ ፈቃድ) ከጠፋ የፖሊስ ማስረጃ
.በካታጎሪው(ደረጃውን) የምመጥን ተሽከርካሪ ማቅረብ መቻል ማቅረብ ካልተቻለ የማሰልተኛ ተቋም ስም ይዞ መምጣት
.2 ጉርድፎቶ 3 X 4
.ከጤናተቋማትየጤናምርመራሰርተፍኬት
የልዩነት ስልጠና ለመውሰድ ማስረጃ ለሚጠይቁና መረጃ ለሚፈለጉ
መረጃውን የጠየቀው አካል ህጋዊ ደብዳቤ
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ (መንጃ ፈቃድ)
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ(መንጃ ፈቃድ) ዕድሳት አገልግሎት ለመስጠት
ከጤናተቋማትየጤናምርመራሰርተፍኬት
የቀድመውንየአሽከርካሪብቃትማረጋገጥፈ
ቃድ(መንጃ ፈቃድ)
ለጠፋ የአሽከርካሪ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ(መንጃ ፈቃድ) ምትክ አገልግሎት ለመስጠት
ቀበሌመታወቂያ/ፓስፖርትየታደሰ
ከፖሊስስለመጥፋቱየአሽ/ብ/ማ/ቁጥርየተገለጸበትደብዳቤ
ለተበላሸ የአሽከርካሪ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ(መንጃ ፈቃድ) ምትክ አገልግሎት ለመስጠት
የተበላሸውንየአሽከርካሪብቃትማረጋገጥፈቃድ(መንጃ ፈቃድ)
መንጃ ፈቃድ ለማደስ
ከባለጉዳይ የሚጠበቅ
1. የአገልግሎት ዘመኑ ያበቃው መንጃ ፈቃድ፤
2.የጤና ማስረጃ ከተፈቀደላቸው ተቋማት፤
3.የአገልግሎት ክፍያ ስድስት መቶ ሃያ (620.00) ብር።
ቅድመ ሁኔታዎችን ካሟሉ የትኛው መስኮት ጀምረው የት እንደሚጨርሱ እዚህ ይመልከቱ
1ኛ.ለሚፈልጉት አገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላትዎትን ያረጋግጡ
ከዚህ https://www.aadvlca.com/help ድህረገጽ ከሚያገኙት መረጃ በተጨማሪ ወደ ቅርንጫፍ ፅ/ቤታችን በር ላይ የተቀመጡ ቅድመሁኔታዎችን እና ለሚፈልጉት አገልግሎት የሚፈጀውን ጊዜ የሚያሳይ የዜጎች ቻርተር በትልቅ ባነር ላይ ተዘርዝሮ ያገኛሉ
በተጨማሪም በርላይ የተለጠፈውን ባርኮድ በስልክዎ በማንበብ ለሚፈልጉት አገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎችንና የባለስልጣን መስሪያቤቱን መተዳደሪያ መመሪያ ማግኘት ይችላሉ
2ኛ. በርላይ እንደገቡ ወደሚያገኙት መስኮት ቁጥር 1 /መረጃ ዴስክ/ ቀርው የወረፋ ትኬት ይቀበሉ
የመረጃ ዴስክ ባለሙያ ያቀረቡት ሰነድ ለሚፈልጉት አገልግሎት ብቁ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ከወረፋ ማስጠበቂያ ማሽን የደረሱበት የወረፋ ቁጥር የሚገልፅ በተጨማሪም ስንት ሰው ከርስዎ በፊት አገልግሎት እያገኘ እንደሆነ የሚያሳይ መረጃ እንዲሁም ትኬትዎ ላይ የታተመውን ባርኮድ በሞባይልዎ አንብበው ሌሎች አገልግሎቶችን እና መመሪያችን የሚያሳይ መረጃ ያገኛሉ
3ኛ.የተዘጋጀልዎ የወረፋ መጠባበቂያ ወንበር ላይ አርፈው ወረፋዎን በድምጽ እና ፊት ለፊት በተሰቀለ ቲቪ ላይ ይከታተሉ
ከርስዎ በፊት ያሉ ሰዎች ተስተናግደው እስከሚጨርሱ ድረስ አርፈው ይጠብቁ
ፊትለፊትዎ የተሰቀለ ቴሌቪዥን ላይ የትኬት ቁጥር እና አገልግሎትዎትን የሚያገኙበት መስኮት ቁጥር እስከሚታይዎትና ክፍሉ ውስጥ በተሰቀሉ ስፒከሮች ቁጥርዎ እስከሚጠራ ድረስ በትግስት ይጠብቁ
4ኛ. ተራዎ ሲደርስ የተጠሩበት መስኮት (ከ6 እስከ 14) ላይ ቀርበው ሰነዶችን በመስጠት አገልግሎት ያስጀምሩ
- አገልግሎትዎ ተሽከርካሪ ማቅረብ እና ቴክኒክ ማስመርመር የማያስፈልግ ከሆነ (ለቦሎ አገልግሎት ፣ለማሳገድ፣ እግድ ለማስነሳት ...)
ተራዎ ሲደርስ የተጠሩበት መስኮት ላይ ቀርበው ሰነዶችን በመስጠት አገልግሎት ያስጀምሩ
አገልግሎት የሚሰጥዎት ባለሙያ ነአገልግሎት ክፍያ እንዲከፍሉ ወደ ገንዘብ ሰብሳቢ ያስተላልፋል
5ኛ. አገልግሎትዎ ተሽከርካሪ ማቅረብ እና ቴክኒክ ማስመርመር የማያስፈልግ ከሆ የአገልግሎት ክፍያ መስኮት ቁጥር 21 ወይም 22 ቀርበው ይክፈሉ
5ኛ. አገልግሎትዎ ተሽከርካሪ ማቅረብ እና ቴክኒክ ማስመርመር የማያስፈልግ ከሆ የአገልግሎት ክፍያ መስኮት ቁጥር 21 ወይም 22 ቀርበው ይክፈሉ
6ኛ. ከከፈሉ በኋላ አገልግሎት ወደጀመሩበት መስኮት ተመልሰው አገለሰግሎትዎንን ይጨርሳሉ
ከከፈሉ በኋላ አገልግሎት ወደጀመሩበት መስኮት ተመልሰው አገለሰግሎትዎንን ይጨርሳሉ