የልደታ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ከጉለሌ ቅ/ፅ/ቤት ጋር የልምድ ልውውጥ በዛሬው እለት አድርገዋል።


ነሐሴ 13/2016

በልምድ ልውውጡም ወደ አምስት የሚጠጉ አገልግሎቶች መስጠት የሚችል Data based የሆነ Soft ware ኪዎስ ማሽኑ ላይ በመጫን ለተገልጋዮች የሚሰጠውን አገልግሎት የበለጠ ቀልጣፋ ማድረግ ፣ የንብረት አስተዳደር ክፍልን የማዘመን፣ የፋይል አደረጃጀትን ማዘመን ፤ ከክልል የሚመጡ ፋይሎችን በሲስተም መቆጣጠር የሚያስችል Software develope ማድረግ፣ የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታ በተለያየ ቋንቋ መረጃ መስጠት፤ ምቹ የስራ ከባቢ መፍጠር፤ የበር መግቢያው ግድግዳ ላይ  Green legacyን ተግባራዊ ማድረግ፣ የደህንነት ካሜራዎችን ስራ ላይ ማዋል ከሪፎርሙ ማግስት ከተሰሩ ስራዎች መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸውን  የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ  አቶ አብይ ዘውዴ ገልጸዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ብልሹ አሰራን ለማክሰም እየሰራ ያለውን  ስራ ወደ ውጤት የቀየረ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አመራሮች ከብልሹ አሰራር የጸዳ እና የዘመነ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ቴክኖሎጂ መጠቀም ዘላቂ መፍትሄ መሆኑን በመረዳት በቅርንጫፉ ለተሰራው ስራ አድናቆታቸውን መግለፃቸው የሚታወስ ነው። ይህንም ከግምት ውስጥ በማስገባት #የልደታ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች በጉለሌ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ቅርንጫፍ በመገኘት ልምድ ወስደዋል።

የልደታ ስራ አስኪያጅ #አቶ ፈጠነ የታየውን ለውጥ በማድነቅ ተቋማቸው የተሻሉ ስራዎችን ለመስራት መዘጋጀቱን በመግለፅ ተሞክሮውን ያካፈሉትን የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ አብይ ዘውዴን እና መላ ሰራተኛውን አመስግነዋል።