ትራንስፖርት ዘርፍ በተመለከ፦
👉በዘርፉ የተለያዩ የአሽከርካሪና የተሽከርካሪ አገልግሎት ፈልገው ለመጡ 1,284,812 ተገልጋዮች የአሽከርካሪነት ብቃት ማረጋገጫና ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ አገልግሎት መስጠት ተችሏል፡፡
👉የሕዝብ ትራንስፖርት አቅርቦትና ፍላጎት ከማጣጣም አንጻር በያዝነው በጀት ዓመት 67 ተጨማሪ አዳዲስ አውቶብሶችን ግዥ በመፈጸም እና በቀን በአማካይ 12,502 የሕዝብ ትራንስፖርት በማሰማራት በየቀኑ ከ3.3 ሚሊዮን በላይ ተሳፋሪዎችን በማጓጓዝ አገልግሎት ተሰጥቷል።
👉የተለያዩ የትራፊክ አደጋ ቅድመ መከላከል ስልቶችን በመተግበር በመንገድ አጠቃቀም ቁጥጥርና ግንዛቤ የማሳደግ፣ የትራፊክ ሲግናሎችን የመትከልና አደባባዮችን የማስተካከል ሥራዎችን በመስራት የትራፊክ ፍሰት እንዲሻሻል ተደርጓል።