የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ሳምንታዊ የስራ ግምገማ እና ከሪፎርሙ በኋላ የተገኙ ለውጦች ላይ በጉለሌ ቅርንጫፍ በመገኘት ውይይት አድርገዋል።
የጉለሌ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብይ ዘውዴ ሪፎርሙ ያስገኛቸውን ትሩፉቶች ሲያስጎበኙ ከዚህ በፊት በሌሎች ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ከተገኙ ተሞክሮዎች በመነሳት በውስጥ አቅም አሰራሩን ዲጂታላይዝድ ለማድረግ በርካታ ስራዎች መስራታቸውን አንስተዋል ።
አገልግሎት የማይሰጡ ማሽኖችን በማደስ ተገልጋዩ እራሱ የሚፈልገውን አገልግሎት መምረጥ፣ ቅድመ ሁኔታዎችን ማወቅ፣ ተገልጋዩ የቅርንጫፋን ዌብ ሳይት በመጠቀም የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ መረጃ በማንኛውም ቦታ ሆኖ በስልኩ መረጃ ማግኘት፣ አገልግሎቱ በደህንነት ካሜራ የታገዘ እንዲሆን ማድረግ፣ ሳምንታዊ የሰራተኞች የስራ አፈፃፀምን መሰረት በማድረግ ምርጥ ፈፃሚዎች የሚለዪበት ሁኔታ መኖሩ በጉብኝቱ ተካቷል።
አገልግሎቱን በቀጥታ በስክሪን መመልከት የሚቻልበት ቴክኖሎጂ ተዘጋጅቶ አገልግሎቱን ፈጣን በማድረግ የተገልጋዬን እርካታ ለማማምጣት የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀው የንብረት ክፍል የመዝገብ ቤት ሰነድ አያያዝና የሰነዶች አወጣጥ ስርዓት የተሻሻሉት ሪፎርሙ ባመጣው የስራ ተነሳሽነት መሆኑን ስራ አስኪያጅ አስረድተዋል።
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ተወካይ እና የቂርቆስ ቅ/ፅ/ቤት ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ደረጄ አሰፋ እንደተናገሩት በጉለሌ ያየነው ተሞክሮ ያለተጨማሪ ወጭ ሰራተኛውን በማስተባበር ፈጣን አገልግሎት መስጠትና ስራውን በውስጥ አቅም ዲጅታላይዝድ ማድረግ እንደሚቻል ተመልክተናል ሰራተኛውን በብቃት በመምራትና በማስተባበር ሪፎርሙን ወጤታማ በሆነ መንገድ ለመሩት ለቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ አመራሮችና ሰራተኛ ምስጋና ይገባቸዋል በማለት በሪፎርሙ የተገኘውን ለውጥ ቀጣይ ለማድረግ ከዚህ የበለጠ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ አስረድተዋል።