አሽ/ተሽ/ፈ/ቁ/ባለስልጣን ጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ሰራተኞችና አመራሮች ለ6 ጊዜ ኮ/ቀራኒዮ ወረዳ 8 ልዩ ስሙ መንዲዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር አካሄዱ።
ተቋሙ ከዚህ ቀደም በተለያዩ አካባቢዎች የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ሲያካሄድ መቆየቱንና ባለፉት 5 ዓመታት በየካ ፓርክ እና መካኒሳ አካባቢ በቋሚነት በርካታ ችግኞች መትከላቸው ተጠቁሟል።
የአሽ/ተሽ/ፈ/ቁ/ባለስልጣን
ጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አቢይ ዘውዴ ከዚህ በፊት ለተተከሉ ችግኞች በቋሚነት እንክብካቤ በመደረጉ
መፅደቃቸውን ገልጸው ይህም በአካባቢው የጎርፍ እና የአፈር መሸርሸርን በመከላከል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን
ጠቅሰዋል።
የአየር ንብረት መዛባት ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ ያለው እንደመሆኑ ተቋማት አስቀድመው የመከላከል ተግባራት ላይ መሳተፍ ይገባልም ብለዋል።
ተቋሙ በክረምት ወራት የአረንጓዴ አሻራ ተሳትፎን በማጠናከር ላይ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በስፍራው በርካታ ችግኞች በተቋሙ አመራሮች እና ሰራተኞች ተተክለዋል።
aadvlca.com