ጤና ይስጥልኝ ዜና እናሰማለን በቅድሚያ አርዕስተ ዜና

ሐምሌ 20/2016ዓ.ም

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በቅርቡ ሪፎርም ማድረጉ ይታወቃል።የሪፎርሙ ውጤታማነት ከሚለካባቸው ዋና ዋና ምሰሶዎች ውስጥ በሰው ኃይል፣ በቴክኖሎጂ፣ በአሰራር፣ በግብዓትና ምቹ የስራ ከባቢ በመፍጠር ሂደት ያለውን አፈጻጸም እና የስራ እንቅስቃሴ በአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በዛሬው እለት እየተገመገም ይግኛል።

በዚህ መነሻነት የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አብይ ዘውዴ  በዛሬው ፕሮግራም ለማዕከል አመራሮች እና ለሁሉም ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ስራቸውን አስጎብኝተዋል። ምቹ የስራ ሁኔታን ለመፍጠር ተግባራትን አቀናጅተው መርተው ወጤት ያስመዘገቡበትንም ሂደት ልምድ አካፍለዋል።

በጉብኝቱም የዘመናዊ ተቋም ግንባታ መዳረሻ የሆነው ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር እና የተቀላጠፈ አገልግሎት ማቅረብ ስኬታማነት ጎልቶ ታይቷል።

ለውጥን በማመን፣ የለውጥ ምክንያት በመሆን፣ በመሰጠት እና ሁሉንም ሰራተኞች ባለቤት በማድረግ እንዲሁም በማሳተፍ፣ በአጭር ጊዜ ውጤታማ ስራ የሰሩትን የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪጅንና ለዚህ ሪፎርም ጉልህ ድርሻ ያላቸውን ሰራተኞችን የባለስልጣኑ የቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች አመስግነዋል።